ስለ እኛ
እንደ ሰው ቤተሰብ አንድ ላይ
እኛ ማን ነን?
ላይደን የስደተኞች ድጋፍ ዴስክ (LSM) ስለ ስደተኞች ህጋዊ ማዕቀፍ፣ ንብረት ነክ ህግጋት፣ ሰብዓዊና ማህበራዊ ጉዳዮች እነዲሁም በህክምና ድጋፍ ዙርያ የሚነሱ ጥያቄዎችን ለመመለስ የተቋቋመ ብዝሃ ባህላዊ፣ ሰብዓዊና ማህበረሰባዊ ድርጅት ነው። ለዚሀም፤ አዲስ መጤ እና መደበኛ ስደተኞች (የስደተኛ ቤተሰቦች፣ በስራ እና ለትምህርት ምክንያት የተሰደዱ) እንዲሁም ሰነድ አልባ ስደተኞች ላይ ትኩረት እንሰጣልን።
ላይደን የስደተኞች ድጋፍ ዴስክ ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት ሲሆን የመኖሪያ ፈቃድ ላላቸው ስደኞች የድጋፍ አገልግሎት በነፃ የሚሠጥ ነው። የመኖርያ ፈቃድ ያላቸው ስደተኞች ከኔዘርላንድስ ስደተኞች ካውንስል (VWN) ከአንድ አመት እስከ ሁለት አመት በኋላ የሚቋረጥ ድጋፍ ሰጪ ተመድቦላቸው ድጋፍ ያገኛሉ። የመኖርያ ፈቃድ የሌላቸው ስደተኞች ግን ድጋፍና ትኩረት ተነፍገው ይቆያሉ። ከVWN፣ UAF ወይም ከመሳሰሉ ለስደተኛ ድጋፍ ከሚያደርጉ ድርጅቶች እምብዛም ድጋፍ አያገኙም።
ለምን ይህን ማረግ አስፈለገን?
LSM የብዝሃ ባህል ማህበረሰብ ዘመናዊ እይታ፣ በተለያዩ ባህሎችና ህዘቦች መስተጋብራዊ ግንኙነት ላይ ሊመሰረት ይገባል ብሎ በጥልቅ ያምናል። እራሳችንን ጤናማ፣ ሰላማዊ ዉይይትና የመጣንበት ቦታ፣ ዘር፣ የቆዳ ቀለም እነዲሁም ሃይማኖት ግንዛቤ ዉሰጥ ሳይገባ እርስ በርስ መከባበር የሠፈነበት ማህበረሰብን ለመገንባት የሚጥር አለማቀፋዊ እንቅስቃሴ አካል አድርገን እናያለን። ራዕያችን “በአንድነት እንደ ቤተሠብ” ሲሆን፤ እኛ አንድ ትልቅ ቤተሠብ እንደሆንንና ምድርም ብቸኛዋ ቤታችን ስለመሆንዋ አሁን ከመቸውም ጊዜ በላይ ግልፅ እየሆነ መጥቷል።
በአረብኛ ቋንቋ እና ባሀል የካበተ ልምድ ያለን ባለሞያዎች ስንሆን በጋራ መግባባት ላይ በተመሰረተ መልኩ የሃገረ ኔዘርላነድስ ጠቃሚ ደንቦችንና ህግጋትን፣ እንዲሁም የመዘጋጃ ቤት (Gemeente) መመሪየዎችንና ዉሣኔዎችን የመተርጎም አገልግሎት እንሠጣለን።
ጥገኝነት ጠያቂዎች፣ መኖሪያ ፈቃድ ያላቸውና ሰነድ አልባ ስደተኞች በአብዛኛው ወደ ኔዘርላንድስ የሚመጡት በጦርነት ከተጠቁ የመካከለኛው ምስራቅና ሰሜን አፍሪካ ሃገራት ሲሆን፤ እኚህ ሰዎች ከባድ ጊዜ የሚያሳልፉ እንዲሁም ከፍትኛ ጫና እና ማህበረሰባዊ መገለል ጭምር ይደርስባቸዋል። በነዚህ ቀጠናዎች በሚገኙ ሃገራት ጦርነት፣ አምባገነናዊ መንግስታት፣ በፖለቲካ አመለካከት ምክኒያት ማሣደድና መሰቃየት እንዲሁም ሃይማኖታዊ ግጭቶች ይስተዋላሉ።
በኔዘርላንድሰ ጥገኝነት የሚጠይቁ ብዙ ስደተኞች በሁኔታዎች መተማመኛ አለማግኘትን ጨምሮ ሕጋዊና የገንዘብ ችግር ያጋጥማቸዋል።
ላይደን የስደተኞች ድጋፍ ዴስክ ሁሉም ሰው ለመብቱ የሚቆምበት፣ እንዲሁም ጤናማ፣ ሠላማዊና ፍትሃዊ ማህበረሰብ ለመገንባት ይጥራል። በተጨማሪም LSM ከአጋር ድርጅቶች ጋር በመተባበር፣ በኔዘርላንድ የሚገኙ ስደተኞችን በሚመለከቱ ጉዳዮች ዙሪያ ሰብዓዊና ፍትሃዊ መፍትሄ ለማምጣት ይሠርል።
LSM አለማቀፋዊ ሰብዓዊ መብቶች ድንጋጌዎችን፣ የአውሮፓ የሰብዓዊ መብቶች ኮንቬንሽንና የኔዘርላንድስ ሃገራዊ ህግጋትን እንደመነሻ ነጥብ የሚወስድ ሲሆን፤ ሰብዓዊ መብቶች ሁለንተናዊ እንደመሆናቸው መጠን ለስደተኞችም በእጅጉ ይገባሉ ብሎ ያምናል። ከዚሀም በተጨማሪ የስደተኞች ጥገኝነት ጥያቄ አያያዝ ሚዛናዊ መሆኑ በጣም አስፈላጊ ነው።
በምን መልኩ ነው የምንቀጥለው?
በኛ አመለካከት ሰበዓዊ መብቶች ሙሉ በሙሉ በህግ የሚቋጩ ጉዳዮች አይደሉም። ስደተኞች መብቶቻቸውን በአግባቡ ይጠቀሙ ዘንድ፣ የሚኖሩበትን ማህበረሰብ አኗኗር በአግባቡ ሊያውቁትና ሊረዱት ይገባል። LSM በዚህ ረገድ የስደተኞችን ከኔዘርላንድ ማህበረሰብ ጋር ለመዋሃድ ለሚያደርጉት ጥረት ድጋፍ በማድርግ፣ እራሣቸውን እንዲችሉና የነቃ ማህበረሰባዊ ተሣትፎ እንዲኖራቸው ይሰራል። ይህን አላማም ከግብ ለማድረስ፣ የህግ ዕውቀትና የተለያዩ ባህሎችና ቋንቋዎች ክህሎት ባላቸው ሰራተኞቹ ይታገዛል።
ምን በማድረግ ላይ እንገኛለን?
LSM በሁለት አይነት መልኩ ለስደተኞች ግልጋሎትን ይሰጣል። በአንድ በኩል፣ የዕለተለት የህግ፣ ማህበራዊና ሰብዓዊ አገልግሎቶች ዙሪያ በአንድ ጊዜ ቀጠሮ ወይም በአጭር ጊዜ ውስጥ ስደተኞች ለሚያጋጥሟቸው መሠረታዊ ችግሮች ዕልባት መስጠት ሲሆን ይህም የማማከር አገልግሎትንና ከአጋር ድርጅቶች ጋር በመተባበር ችግሮችን መፍታትን ያካትታል። በሌላ በኩል ደግሞ፣ ሒደት ተኮር በሆኑ ሕግ እና ማህበራዊ ጉዳዮች ዙሪያ በማተኮር የድጋፋችን ተጠቃሚ የሆኑት ስደተኞች የሚያጋጥማቸውን ችግር በመለየት ተገቢውን ድጋፍ የሚያገኙበትን መንገድ ማመቻቸት።
የምንሰጣቸው ድጋፎች፡-
- መረጃዎችን መሰብሰብና ለስደተኞች የምክር አገልግሎት መስጠት። ለምሣሌ፡ የጥገኝነት ጥያቄ አካሄድን አሰመለክቶ የሚነሱ ጥያቄዎች አስመልክቶ፣ የገንዘብ ዕዳ ጉዳዮችና የተለያዩ ማህበራዊ ሁኔታዎችን አስመልክቶ ማማክር፣
- ሰልጠናን ጨምሮ በተለያዩ ህጋዊ ጉዳች የስራ እድልን አስመልክቶ የመረጃ ልውውጥ የሚካሔዱባቸውን የምሽት መድረኮችን ማዘጋጀት። አዲስ መጤዎች የኔዘርላንድ ማህበረሰብን አኗኗር በተቻለ ፍጥነት ሊረዱት ይገባል፣
- የመኖሪያ ፈቃድ ላላቸውም ለሌላቸውም ስደተኞች እንዲሁም ለስደተኞች ቤተሰቦች የጥገኝነት ጥያቄ አካሔድን አስመለክቶ ህጋዊ ድጋፍ መስጠት፣
- የሃገረ ኔዘርላንድስ ጠቃሚ ደንብና ህግጋትን፣ እነዲሁም የመዘጋጃ ቤት መመሪየዎችንና ዉሣኔዎችን ወደ አረብኛና ወደ ተለያዩ ቋንቋዎች መተርጎም፣
- ጠቃሚ የአረብኛ ሃሳቦችንና አገላለፆችን ወደ ደች ቋንቋ መተርጎም፣
- ማህበራዊ፣ ባህላዊና ጥበባዊ መድረኮችን በማዘጋጀት በተለያዩ ባሀሎችና ህዝቦች መካከል መቀራረብ መፍጠር፣
- በላይደንና አከባቢዋ ከሚኖሩ አረብኛ ተናጋሪ ከሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎች ጋር ለሚሰሩ ድርጅቶች የአረብኛ ቋንቋ መረጃ መስጫ ምሽቶችን ማዘጋጀት።