LMS ፕሮጀክት-ድልድይ ትምህርት
ስለ ፕሮጀክቱ
ሕፃናትና ወጣቶች ከሃገራቸው ከተሰደዱና በባዕድ ሃገር ጥገኝነት ከጠየቁ በኋላ ለዘርፈ ብዙ ችግሮች ይጋለጣሉ። ከነዚህም ችግሮች ዉሰጥ አንዱ የትምህርት መቋረጥ ነው። የባከኑ የትምህርት አመታትና አዲስ ቋንቋ መማር ትልቅ እክሎች ሆነው ተነሳሽነት ለማጣትና ለበታችነት ስሜትም ይዳርጋሉ። ከዚህም በተጨማሪ ስደተኞቹ የሚመጡበት ሃገርና በተቀባይ ሃገር የሚገኘው የትምህርት አሰጣት ዘይቤ መሃከል ላለው ልዩነት ያልተዘጋጁ መሆናቸውም ለላቀ ችግር ሲዳርጋቸው ይስተዋላል።
ጥገኝነት ጠያቂዎች፣ መኖሪያ ፈቃድ ያላቸውና ሰነድ አልባ ስደተኞች በአብዛኛው ወደ ኔዘርላንድስ የሚመጡት በጦርነት ከተጠቁ የመካከለኛው ምስራቅና ሰሜን አፍሪካ ሃገራት ሲሆን፤ እኚህ ሰዎች ከባድ ጊዜ የሚያሳልፉ እንዲሁም ከፍትኛ ጫና እና ማህበረሰባዊ መገለል ጭምር ይደርስባቸዋል። በተቋማችን ዕምነት የሕግ ከለላ እና የመኖያ ፈቃድ ማግኘት በቂ ናቸው ብለን አናስብም። ስደተኞች ከሚኖሩበት ማህበረሰብ ጋር በድምብ መዋሃድና የማህበረሰቡን አኗኗር ማወቅ በጣም አስፈላጊ ነው ብለን እናስባለን።
ምንም እንኳን ሕፃናት በቀላሉ የመላመድ አቅም ቢሮራቸውም፣ አዋቂ ስደተኞች ለዘመናት ከገነቡት ሕይወታቸው ለመለየትና ከአዳዲስ ዕዉነታዎች ጋር ለመጋፈጥ ይገደዳሉ። አዳዲስ ህግጋት ማወቅና መከተል፣ በባእድ ሃገር ቋንቋ መግባባትና በማህበራዊ ሕይወት ውስጥ ያለረዳት የራሳቸው የሆነ ቦታን ለማግኘት ይቸገራሉ። ፕሮጀክቱ ሕጻናትና ወጣቶች በስደት ምክኒያት የቋረጡትን ትምህርት እንዲቀጥሉና ከኔዘርላንድ ሃገር የትምህርት ስርዓት ጋር እንዲላመዱ ድጋፍ ለማድረግ ያለመና በቤት ውስጥ በደች ቋንቋ አቅም ማጣት ምክኒያት ወላጆቻቸው ሊያስጠኗቸው ያልቻሉ ተማሪዎችን የሚያግዝ ነው።
LSM ለስደተኛ ተማሪዎች በግለሠብ ደረጃ ባህሎችን የማቀራረብና በትምህርት ረገድ ያሉ ክፍተቶችን ለመሙላት ይጥራል። በዚህም፣ ታዳጊ ስደተኞች ቀድሞ በሃገራቸው ከሚያዉቁት የትምህርት ስርዓት ወደ ተሰደዱበት ሃገር አዲስ የምህርት ስርዓት የሚያደርጉትን ሽግግር በመደገፍ፣ በተምህርታቸው የነቃ ተሳትፎ የሚያደርጉ እንዲሁም በራስ መተማመን የተሞሉ ለማድረግ ይሰራል።
ይህ ፕሮጀክት የ LSM በኔዘርላንድ የሚገኙ ታዳጊ ስደተኛ ተማሪዎችን የትምህርት ሂደት የመደገፍ ፍላጎት የመነጨ ሲሆን፣ በአለማቀፍ ተማሪዎችና በበጎ ፍቃደኞች የሚተገበር ይሆናል። ባሁኑ ወቅት ትኩረት የምናደርገው በሒሳብ ትምህርት፣ በእንግሊዘኛ፣ ፈረንሳይኛ እና ጀርመንኛ ቋንቋዎች ሲሆን በቀጣይ ተጨማሪ የትምህርት አይነቶችን የመጨመር ዕቅድ አለን።
ለትምህርት ክፍሎች እንዴት ማመልከት እንደሚቻል
የምዝገባው ሒደት እንደሚከተለው ይሆናል፡
- ልጆች ወይም ወላጆቻቸው በመሙላት መመዝገብ ይችላሉ ይህ የምዝገባ ቅጽ።
- የ LSM ባልደረባ ፍላጎት ካሳዩ ተማሪዎች ጋር የመጀመሪያ ቃለመጠይቅ በማድርግ መስፈርቶች መሟላታቸውንና የተማሪዎቹ ፍላጎት ምን እንደሆነ የመለየት ስራ ይሰራል። ተማሪው/ዋ ድጋፍ ሊሠጠው/ት እንደሚገባ ከታመነ፣ ከአስጠኚ ጋር የማጣመር እና የጥናት ቡድን ዉስጥ የመመደብ ስራ የሰራል።
- የጥናት ክፍለ ጊዜዎቹ ማክሰኞ እና እሁድ ከሰዓት ወይም ማምሻውን የሚሆን ሲሆን ወደፊት ተጨማሪ ክፍለጊዜዎች እናክላለን የሚል ሃሳብ አለን።